BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ቀጥታ, እስራኤል በቴህራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የኢራን ሚሳኤሎች በእስራኤል ጉዳት አድርሰዋል
የእስራኤል ጦር በኢራን የኒውክሌር መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት ፈጽሜያለሁ ካለ በኋላ ኢራን ወደ እስራኤል ያስወነጨፈቻቸው ሚሳዔሎች ጉዳት ማድረሳቸው ተሰማ።
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ?
ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላማዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአራት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ?
እስራኤል በኢራን በፈጸመችው ጥቃት የተገደሉ የጦር አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶች እነማን ናቸው?
እስራኤል ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ በመላው ኢራን ባሉ የኒውክሌር ይዞታዎች፣ ወታደራዊ ስፍራዎች እና የመኖሪያ ስፍራዎች ላይ በፈጸመቻቸው በርካታ ጥቃቶች ከፍተኛ የጦር አዛዦች እና ስድስት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ተገድለዋል።
አዛዦቹ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉበት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ማን ነው? ምንስ አቅም አለው?
እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በርካታ የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸውን ኢራን አረጋግጣለች። በጥቃቱ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የአየር ኃይል አዛዥን ጨምሮ ቢያንስ 20 የኢራን ወታደራዊ ኃይል ከፍተኛ አዛዦች ተገድለዋል። ይህ ኢራን የምትመካበት ወታደራዊ ኃይል ማን ነው? ምንስ አቅም አለው?
የተከሰከሰውን የሕንድ አውሮፕላን የበረራ መረጃዎች የያዘው ጥቁር ሳንዱቅ ተገኘ
ኤር ኢንዲያ እንዳለው በቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑ 169 የሕንድ፣ 53 የእንግሊዝ፣ ሰባት የፖርቹጋል እና አንድ የካናዳ ዜጎች ተሳፍረው ነበር።
የኬንያ የፖሊስ ኃላፊ በጦማሪው ግድያ ታሰሩ
በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኝ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳለ ከተገደለው ወጣት ጦማሪ ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን ገለልተኛ መርማሪዎች ገለጹ።
እስራኤል እና ኢራን በወታደራዊ አቅም ምን ያህል ተመጣጣኝ ናቸው?
ኢራን እና እስራኤል ለረጅም ጊዜ በእጅ አዙር እንጂ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ገብተው አየውቁም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንደኛው በሌላኛው ላይ የቀጥታ ጥቃት እየፈጸሙ ከጦርነት አፋፍ ላይ መድረሳቸው አሳሳቢ ሆኗል። ለመሆኑ እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል? ሁለቱ አገራትስ በወታደራዊ አቅም ምን ያህል ይመጣጠናሉ?
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
በፌደራል መንግሥት የ2018 በጀት ውስጥ ለአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ ሳይካተት ቀረ
በቀጣይ ዓመት የፌደራል መንግሥት አጠቃላይ በጀት ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሳይካተት ቀረበ። በቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ ለክልሎች እና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተመደበው የፌደራል መንግሥት የበጀት ድጋፍ፤ ከዘንድሮው ጋር ሲነጻጸር በ92 ቢሊዮን ብር አድጓል።
በሶማሌ ክልል "የመገንጠል ስሜት ቀርቷል ማለት ይቻላል" - ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ መሐመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በቅርቡ በኬንያ ተገኝተው ከሶማሊ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር እንዲሁም ከባለሥልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል። አቶ ሙስጠፌ ናይሮቢ በነበራቸው ቆይታ ከቢቢሲ ሶማሊኛ እና ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎቶች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።
ህወሓትን በመቃወም የትጥቅ እንቅስቃሴ የጀመሩት ጄነራል ምን ይላሉ?
በህወሓት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ የድርጅቱን አመራሮች በመቃወም ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ የገቡ የሠራዊቱ አባላት እንዳሉ ሲነገር ቆይቷል። ይህ ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ ያመራው ቡድን ዓላማው ምንድን ነው? እነ ማንስ ይሳተፉበታል?
ዐቃቤ ሕግ በሙዚቀኛ አንዱዓለም ጎሳ ላይ ክስ ባለመመሥረቱ በዋስ መፈታቱን ጠበቃው ገለጹ
በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የነበረው ሙዚቀኛ አንዱአለም ጎሳ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ ባለመመሥረቱ በዋስ መለቀቁን ጠበቃው ሊበን አብዲ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድገት ሳይሆን 'ሚራክል' ነው ያለው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው "ዕድገት ሳይሆን ሚራክል [ተዓምር] ነው" ሲሉ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ምጣኔ ኃብታዊ ጉዳዮች ላይ በተናገሩበት ቃለ ምልልሳቸው የሠራተኞች የደመወዝ ጥያቄን አንስተዋል።
በመንግሥት ብቻ በነጻ ይሰጥ የነበረው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በክፍያ ሊሆን ነው
መንግሥት ለተጠቃሚዎች በነጻ ይሰጥ የነበረው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በክፍያ እንዲሆን እና የግል ዘርፍ ተዋንያን እንዲሳተፉበት የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 19/2017 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ "ባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር" አዋጅ ይሰኛል።
የኤርትራ ወታደሮች የያዟቸውን ግዛቶች "እነሱ ያውቋቸዋል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች እንዲያስወጣ ዓለም አቀፉ ማኅበረብ ጫና እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረቡት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ የያዟቸውን ግዛቶችን በተመለከተ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "እነሱ ያውቋቸዋል" ሲሉ ተናገሩ።
የታሰሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል "በቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ" ስምምነት ተፈረመ
ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የሚገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ተሰማ "ከእስር እንዲፈቱ" የሚያስችል ስምምነት በክልሉ መንግሥት እና በተቃዋሚው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) መካከል መፈረሙ ተገለጸ።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
በቀን ምን ያህል ውሃ መጠጣት አለብን? ውሃ በሰውነታችን ውስጥ ሲያንስ እና ሲበዛ ምን ይከሰታል?
ውሃ ለሕይወት አስፈላጊ ነው። በርካታ ዓለም አቀፍ መመሪያዎች አንድ ሴት በቀን ሁለት ሊትር፣ ወንድ ደግሞ 2.5 ሊትር ውሃ ቢጠጣ ለጤና መልካም መሆኑን ይመክራሉ።በቂ ውሃ አለመጠጣት ለድርቀት ያጋልጣል። ከዚያ በተቃራኒ ደግሞ ብዙ ውሃ መጠጣትም አደገኛ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ እና የዕለት ምግባችንን ምን ያገናኛቸዋል?
የሳይንስ ሊቃውንት አመጋገባችንን ብንቀይር እና የሥጋ እና የወተት ተዋጽፆዎችን በዕፅዋት ምግቦች በመተካት የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ይረዳል ሲሉ ቆይተዋል። የዓለምን ሕዝብ የአመጋገብ ሥርዓትን መቀየር ግን ቀላል አይደለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያ በምግብ እና በአየር ንብረት ለውጥ መካከል ስላለው ግንኙነት በሐሰተኛ እና በአሳሳች መረጃዎች ተሞልቷል። ዋና ዋናዎቹን ጉዳዮች እንደሚከተለው ቃኝተናቸዋል።
ጉግል ለምን ‘ማንበብ የምንፈልገውን’ መረጃ አዘውትሮ ያቀርብልናል?
ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ጉግል የምንፈልገውን ዓይነት መረጃ ነው የሚሰጠን። ለኛ ዕሳቤ ቅርብ የሆኑ መረጃዎችን በማቅረብ ሐሳባችንን ያጠናክራል።ለመሆኑ ጉግል ለምን ‘መስማት የምንፈልገውን’ መረጃ አዘውትሮ ያቀብለናል?
ቡና መጠጣት ለጤና ጠቃሚ ነው ጎጂ? በምን ያህል መጠን?
ቀደም ባሉት ጊዜያት ቡና ከጤና እክሎች ጋር ተያይዞ ስሙ በክፉ ይነሳ ነበር። ነገር ግን ባለፉት አስርት ዓመታት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቡና መጠጣት ለጤና በረከት ሊሆን ይችላል። ሰዎች ለዘመናት ተፈጥሯዊ የካፌይን ምንጭ የሆነውን ቡና ሲጠጡ ቢቆዩም በጤና ላይ አለው ተብሎ ከሚናፈሰው አሉታዊ ወሬ ጋር ተያይዞ ለአስርት ዓመታት እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ መልዕክቶች ሲተላለፉ ቆይተዋል።
ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ በሚያደርጉት ድብቅ ጦርነት ኪም ጆንግ ኡን እያሸነፉ ነው?
ደቡብ እና ሰሜን ኮሪያን የሚለየው አጥር የኤሌክትሪክ ገመድ አለው። ይህን አጥር የሚጠብቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችም ተደርድረዋል።
የሥራ ማቆም አድማ በኢትዮጵያ ከትላንት እስከ ዛሬ . . .
የኢትዮጵያ ሠራተኞች መደራጀት፣ የተሻለ ደመወዝ፥ የሥራ እና የኑሮ ሁኔታዎችን እንዲመቻቹላቸው መጠየቅ ከጀመሩ ስድስት አስርት ዓመታትን አስቆጥረዋል። በእነዚህ ዓመታት ጥያቄዎቻቸው ጆሮ እንዲያገኙ ከሥራ ማቆም አድማ ጀምሮ የአደባባይ ተቃውሞ እስከ ማድረግ የደረሱ የትግል ስልቶችን ተጠቅመዋል። ነገር ግን እነዚህ የሥራ ማቆም አድማዎች ምን አስገኙ? ምንስ ገጠማቸው?
"በሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለማጥናት 200 ሺህ ዶላር አሰባስቤያለሁ" የትራምፕ ፖሊሲ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታት አፍሪካዊት
ፋጡ ውሬ፣ ቤተሰቦቿ እና ወዳጆቿ በአሜሪካ ውስጥ ስመ ጥር በሚባለው ሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርቷ ለመክፈል 200 ሺህ ዶላር አሰባስበዋል።
ለአእምሮ ጤና እና ደስተኛ ለመሆን የሚያግዙ አራት መንገዶች
ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ ሰውነትዎ ዶፓሚን፣ ኦክሲቶሲን፣ ሴሮቶኒን እና ኢንዶርፊን የተባሉትን አራት ሁነኛ ሆርሞኖች ይፈልጋል።ሁሉም ሰው በሕይወት ዘመኑ የሆነ ወቅት ላይ ከአእምሮ ጤና ጋር ችግር መግጠሙ አይቀርም። ነገር ግን የሰውነትን ኬሚስትሪ ሚዛን ለመጠበቅ እና ደኅንነትን ለመጠበቅ ሊደረጉ የሚችሉ ትናንሽ፣ ነገር ግን ተግባራዊ እርምጃዎች አሉ።
አጃኢብ!
መድኃኒት የሚቋቋሙ አደገኛ ተህዋሲያንን ለማስወገድ ከዓይነ ምድር የተሠራ እንክብል ሙከራ ላይ ዋለ
የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች በበረዶ የደረቀ የሰው ዓይነ ምድርን የያዙ 'ፑ ፒልስ' (poo pills) የተባለ እንክብልን በመጠቀም መድኃኒትን የሚቋቋሙ አደገኛ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን ለማከም እየሞከሩ ነው።
በፍቅር አጋሩ መጠጥ ላይ የጽንስ ማቋረጫ እንክብል 'የጨመረው' አሜሪካዊ በግድያ ወንጀል ተከሰሰ
የፍቅር አጋሩ ሳታውቅ መጠጧ ላይ የጽንስ ማቋረጫ እንክብል ጨምሯል የተባለው አሜሪካዊ በግድያ ወንጀል ተከሰሰ።
ቪዲዮ, በቀን ሦስት ሚሊዮን ሰዎችን ለማስተናገድ የሚችለው የመካው ታላቁ መስጂድ, ርዝመት 2,08
ሚሊዮኖች በየዓመቱ ወደዚህ ስፍራ ለሐጅ ጉዞ የሚሄዱ ሲሆን፣ ይህ ታላቁ መስጂድ ባለፉት ሰባ ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት አስፈልጎታል በዚህም በቀን አስከ ሦስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አለው። ይህ በካዓባው ዙሪያ ያለው ታላቁ መስጂድ እየተስፋፋ ከየት ተነስቶ አሁን ካለበት ደረሰ? በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለማስተናገድስ ምን ያህል አቅም አለው?
ሩሲያን ድል እያቀዳጀ ያለው 'ፋይበር ኦፕቲክ' ድሮን
የፋይበር ኦብቲክ' ድሮን 'ጭራ' ላይ በ10 ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ ገመድ ይጠመጠምባቸዋል። በሌላኛ ጫፍ ድግሞ ድሮኑን ከሚቆጣጠረው መሳሪያ ጋር ይገናኛሉ። "ወደ ድሮኑ የሚመጣውም ይሁን ከድሮኑ የሚወጣው ቪዲዮና የቁጥጥር ሲግናል የሚተላለፈው በኤሌክትሪክ ገመዱ (ኬብል) አማካኝነት እንጂ እንደሌላው ድሮን በሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ አይደለም። ይህ ማለት በኤሌክትሮኒክ የመከላከያ ሥርዓት የድሮኑን ጉዞ ማጨናገፍ አይቻልም ማለት ነው" ሲል አንድ የዩክሬን ድሮን ማሃንዲስ ነግሮናል።
ለልጆቻችን ዕድገት እና የአእምሮ ጤና ጠቃሚ መሆኑ እየተነገረለት ያለው ንጥረ ነገር
ኮሊን የተባለው ንጥረ ነገር ለሰውነት ጠቃሚ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳል። ኮሊን የሰው ልጆች አእምሮ በአግባቡ እንዲሠራ ይረዳል። የማሰላሰል ብቃትን በማሻሻል ከአእምሮ ዕድገት ጋር የተያያዙ ህመሞችን በመከላከልም እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ።
ደንበኞች የሚፈልጉትን አንስተው በታማኝነት ከፍለው የሚገለገሉበት ጠባቂ አልባ ሱቆች
በእኩለ ሌሊት የሚቀመስ ነገር ለሻተ በደቡብ ኮሪያ መዲና ሴዑል የሚገኙ ሱቆች በሮቻቸውን ክፍት አድርገው ይጠብቃሉ። እነዚህ ሱቆች 24 ሰዓት ነው የሚያገለግሉት። ነገር ግን ሱቆችን የሚጠብቅም ሆነ ገንዘብ የሚቀበል ሰው የለም። ሰዎች ወደ ሱቆቹ ገብተው የፈለጉትን ካነሱ በኋላ በታማኝነት ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ከፍለው ይወጣሉ።
ቪዲዮ, ማክሮን በአደባባይ የተገፈተሩት 'ለቀልድ' እንጂ የቤት ውስጥ ጸብ አይደለም አሉ, ርዝመት 0,35
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለጉብኝት ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የሆነው በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል። የአውሮፕላኑ በር ተከፍቶ ፕሬዝዳንቱ ፊት ለፊት በሚታዩበት ጊዜ አንድ እጅ ጸብ በሚመስል ሁኔታ ፊታቸውን በኃይል ሲገፋ ታይቷል። በዚህ ጊዜ ፕሬዝዳንቱ ምንም እንዳልተፈጠረ የእጅ ሰላምታ ሰጥተው ሚስታቸውን ከጎናቸው በማድረግ ከአውሮፕላኑ ወርደዋል።
ለውበት ሲባል የሚደረግ ቀዶ ሕክምና ፡ "100 የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና አድርጌያለሁ፤ ከዚህ በኋላም እቀጥላለሁ"
ከገቢ መጨመር እና የማኅበረሰባዊ አስተሳሰብ መለወጥ ጋር በተያያዘ በአንድ ወቅት እምብዛም የማይደገፈው የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ባለፉት 20 ዓመታት በቻይና እየተለመደ መጥቷል። 80 በመቶ ታካሚዎች ሴት ሲሆኑ፣ ዕድሜያቸው በአማካይ 25 ይደርሳል። በቻይና ባህል ውበት ከፍ ያለ ዋጋ ቢኖረውም ቆንጆ ተብሎ የሚወሰደው መልክ እየተለወጠ መጥቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
የጣራ እና ግድግዳ እርጥበት ለአስም እና ለካንሰር ሊያጋልጠን እንደሚችል ያውቃሉ?
በሻጋታ ምክንያት የሚከሰት ቶክሲን የተባለ መርዛማ ኬሚካል ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትል ሲሆን፣ የመተንፈሻ አካላትን ከመጉዳቱም በላይ ለካንሰርም ሊያጋልጥ ይችላል ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ። የቤት ውስጥ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ሻጋታ ገዳይ መርዝ የማመንጨት ኃይል አለው።
ዓለማት ለምን እና እንዴት እንደተፈጠሩ ለማወቅ እየጣሩ ያሉት የ30 አገራት ሳይንቲስቶች
የሰው ልጅ ምድር በምትባለው ፕላኔት ላይ መኖር ከመጀመሩ በፊት የሆነው ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከ30 አገራት ሳይንቲስቶች ተሰባስበዋል። በአሜሪካ በሚገኝ አንድ ቤተ ሙከራ ውስጥ የሳይንስ ሊቃውንት ለአንድ ትልቅ ሳይንሳዊ ጥያቄ መልስ እየፈለጉ ነው። ጥያቄው አጽናፈ ዓለማት ወይንም ዩኒቨርስ ለምን ተፈጠሩ?
ከእርግዝና ውጪ የወር አበባ እንዲቀር የሚያደርጉ ስምንት ምክንያቶች
የወር አበባ መቅረት (amenorrhea) በብዛት ከእርግዝና ጋር ይተሳሰራል። ሆኖም ግን እርግዝና ሳይፈጠርም የወር አበባ የሚቀርባቸው ምክንያቶች አሉ። የወር አበባ አልፎ አልፎ ቢቀር እንደ ችግር ባይወሰድም በተደጋጋሚ ከተከሰተ መነሻ ምክንያቱ መታወቅ አለበት።
"ራሴን ለማጥፋት ጫፍ ላይ ደርሼ ነበር፤ አሁን ግን ሌሎችን እረዳለሁ"
በዓለም የጤና ድርጅት መሠረት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከአምስት ሴቶች አንዷ ከወሊድ በኋላ የአእምሮ ጤና መታወክ፤ በዋነኛነት የመንፈስ ጭንቀት ያጋጥማታል። የሆርሞን ለውጦች እንዲሁም ስቃይ የበረታበት ወሊድ፣ ድህነት ወይም ሐዘን የመሳሰሉ ጭንቀቶች በእርግዝና ወቅት እና ከእርግዝና በኋላ በአእምሮ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
ኤአይ ያፈቅራል? ያዝናል? የኅልውና ስጋት ነው?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት በሰው ልጆች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊኖረው እንደሚችል እየተነገረ ነው። በተጨማሪም ‘ሰዋዊ’ ሊባሉ የሚችሉ ድርጊቶች ሊከውንም ይችላል እየተባ ሲሆን፣ አንዳንዶች ለሰው ልጆች ህልውና ስጋት ነው ይላሉ። ዕለት ከዕለት እየተራቀቀ የመጣው ሰው ሠራሽ አስተውሎት ማፍቀር እና ማዘንን የመሳሰሉ የሰው ልጆች ውስጥ የሚፈጠሩ ስሜቶችን ሊያሳይ ወይም ሊላበስ ይችላል?
ተመራማሪዎች የወፍ ጉንፋን ቀጣዩ የዓለማችን ወረርሽኝ ይሆናል ብለው ለምን ሰጉ?
ተመራማሪዎች ለወራት በእርሻዎች ላይ እየተስፋፋ ያለው የወፍ ጉንፋን ቀጣዩ የዓለም ወረርሽኝ ይሆናል በሚል የማስጠንቀቂያ ደወል እያሰሙ ነው። በሽታዎች እንዴት እንደሚጎለብቱ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች የወፍ ጉንፋን ልብ ሳንለው ወደ ሰዎች በመዛመት ወረርሽኝ ይሆናል በማለት አስጠንቅቀዋል።
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
ይህ ከ40ዎቹ የዕድሜ ክልል በተሻገሩ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የካንሰር ዓይነት በተመለከተ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች እዚህ ቀርበዋል። የፕሮስቴት ካንሰር ምንድን ነው? ማን የበለጠ ተጋላጭ ነው? መከላከል ይቻላል? መልክቶቹ ምንድን ናቸው? ሕክምናስ አለው?
በዓለም ዙሪያ የኦቲዝም ክስተት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል? ወይስ ሌላ ምክንያት አለ?
ኦቲዝም ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እየታወቀ እንዲሁም ሰዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ምርመራ እያደረጉ ነው። ይህ ግን ኦቲዝም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤም ፈጥሯል።
ሌላ ዕይታ
ከማኅደራችን
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከበሮ እና ጽናጽልን ሌሎች ቤተ እምነቶች እንዳይጠቀሙ መከልከል ትችላለች?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የከበሮ፣ ጽናጽል እና መቋሚያ ንድፎችን በአዕምሯዊ ንብረትነት ማስመዝገቧን ተከትሎ ጉዳዩ ሲያከራክር ሰንብቷል። ምዝገባው ሌሎች ቤተ እምነቶች እነዚህን መገልገያዎች “እንዳይጠቀሙ የመከልከል መብት ይሰጣል ወይስ አይሰጥም?” የሚለው የክርክሩ ማጠንጠኛ ሆኗል። በዚህ ጉዳይ ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ኃላፊዎች ያላቸው አረዳድ እና የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን አቋም የተለያየ ነው።
ዕድገት በኅብረት ዘመቻ፡ የሦስቱ ጓደኛሞች የ50 ዓመታት ትዝታ
ወታደራዊው አስተዳደር ደርግ የአገሪቱን የመሪነት መንበር ከያዘ በኋላ የዛሬ 50 ዓመት የዕድገት በኅብረት ዘመቻን አወጀ። በዚህም ከ10ኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች እና መምህራን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተሰማርተው በማስተማር እና በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ አድርጎ ነበር። በዚህ ዘመቻ የተሳተፉ የዚያ ዘመን አፍላ ወጣቶች ከአምስት አሥርታት በኋላ በጋራ ተሰባስበው ያሳለፉትን ጊዜ አስታውሰዋል። ትዝታቸውንም ለቢቢሲ አጋርተዋል. . .
የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ
ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት። ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን። ኦቲስቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
የኢየሱስ ስቅለት እና ሞት በሕክምና ባለሙያዎች ዓይን እንዴት ይተነተናል?
በአይሁዶች እና ሮማውያን ችሎት ወንጀለኛ ተብሎ የቆመው ኢየሱስ ክርስቶስ በጥፊ ተመትቷል፣ ተገርፏል፣ ተራቁቷል፣ የእሾህ አክሊል ተደፍቶበታል። ኢየሱስ ከተያዘበት እስከ አርብ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ስቃይ ደርሶበታል። በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ብዙ ደም ፈስሶታል። ተጠምቷል። ከዚያም ሞቷል። የሕክምና ባለሙያዎች ኢየሱስ የደረሰበትን እንግልት፣ ድብደባ እና ስቅላት ከሙያቸው አንጻር እንዲህ ተንትነውታል።
'ዝምተኛው ገዳይ' በኢትዮጵያ
የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ልኬት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። ድርጅቱ እንደሚለው 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚዳርገው የአየር ብክለት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ ይናገራሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዋነኛ አየር በካዮች የትኞቹ ናቸው? መፍትሔውስ ምንድን ነው?
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ክፉኛ አቁስላ፣ ማርካ ያከመችው የጁባላንዱ ፕሬዚዳንት ማዶቤ
"የብዙ ኢትዮጵያዊ ደም ነው የወሰደው። የኢትዮጵያ ደም ነው ያለህ እንለዋለን" ይህ በሶማሊያ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለአሁኑ የጁባላንድ ግዛት ፕሬዚዳንት ማዶቤ በቀልድ መልኩ ጣል ያደርጉላቸው ነገር ነው። ይህ በቀልድ የተለወሰ መሪር እውነታ ነው። እውነታው የሶማሊያዋን ራስ ገዝ ጁባላንድን ላለፉት 12 ዓመታት ያስተዳደረው ማዶቤ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ጦር ክፉኛ ቆስሎ በአዲስ አበባ ህክምና አድርጓል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?